Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

doee

DOEE
Menu

Amharic (አማርኛ)

This page contains information about DOEE's services for Amharic speakers.
For more information on the Language Access Program visit the Office of Human Rights.

የኤጀንሲ ስም፡ (የዲስትሪክት የአከባቢ ዲፓርትመንት (Department Energy and Environment)
ተልዕኮ፦ የዲስትሪክት የአከባቢ ዲፓርትመንት (ዲዲኦኢ))ተልዕኮ፣ አካባቢውን በመንከባከብ እና በመተካት፣ የተፈጥሮ ሀብታችንን በመጠበቅ፣ ብከላን በመቀነስ እና ለፊደፊቱ ዘላቂነትን ለማረገጥ እንዲችል የሚያረጉትን ዘይቤዎች ህብረተሰቡን በማስተማር፣ የዋና ከተማይቱን ተቀማጮች እና ነዋሪዎች የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ነው።

ዋና ፕሮግራሞች/የክፍሎቹ ገለጻ፦ የዳሬክተሩ ቢሮ የዲስትሪክቱ የአካባቢዎች ጥበቃ ግቦች በስኬት እንዲመቱ ለማድረግ የኤጀንሲውን አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች በበላይነት ይቆጣጠራል። ከኤጀንሲ-አቀፍ ቀደምት-ጉዳዮች በተጨማሪ፤ የዳሪክተሩ ቢሮ የኤጀንሲው ውስጣዊ አስተዳደር፣ ኤጀንሲውን በኢኮኖሚያዊ እድገት ፕሮጀክቶች ላይ ያለውን ሀላፊነት እና ሚናዎች፣ የህግና የደንብ ጉዳዮችን እና የህዝባዊ ጉዳዮችን ማስተባበር ላይ የሚያተኩር ተነሳሽነትን ይጨምራል። ከከንቲባው ዋና ቀደምት-ጉዳዮች አንዱ በዳሬክተሩ ቢሮ የሚካሔደው እና

በዕቅድ እና ቀጣይነት ቢሮ (ኦፒኤስ)((Office of ድጋፍ ስር የሚሰራው “ዘላቂ ዲሲ (Substainable DC)” ነው ። በተጨማሪ፣ ኦፒኤስ(OPS) የዲስትሪክቱ አከባብያዊ ተግዳሮቶችን የሚፈታ እና ዘላቂነትን የሚያዳብር ዘመናዊ የዕቅድ እና የፕሮግራም መፍትሔዎች ያዘጋጃል። ኦፒኤስ (OPS) ከእህት ኤጀንሲዎች፣ ከከንቲባው ቢሮ፣ ከዲሲ ካውንስል እና ከሌሎች ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርችቶች እና ግለሰቦች ጋር በመሆን መጠነ ሰፊ የሆኑ ዘላቂ አካሄዶችን እዲዘወተሩ በሚያደርግ፣ እንደነ አረንጓዴ ህንጻ፣ አረንጓዴ መሰረተ ልማት፣ የዘለቂነት ዕቅድ፣ እና አረንጛዴ ቤት የጋዝ ስርጭት መጠን መቀነስን የመሳሰሉ ፕሮግራሞች እና ግንኙነቶችን ያስተባብራል።

አስፈጻሚ እና የአከባብያዊ ፍትሕ ቢሮ (ኦኢኢጄ)የዲዲኦኢ(DOEE) የማስፈጸሚያ ሙከራዎችን የሚረዱ ውጤታማ አሰራሮችን ያዳብራል። ኦኢኢጄ (OEEJ)፣ ስልጠናን በመስጠት፣ መደበኛ የስራ መርሆችን በማውጣት፣ ሰነዶች በመያዝ፣ እና የሲቪል መሰረተ ልማት ፕሮግራሞችን በማካሔድ በቀጥታ ከዲዲኦኢ(DOEE) አከባብያዊ ማስክበር ፕሮግራም ጋር ይሰራል። ኦኢኢጄ(OEEJ)፣ ከዩ.ኤስ. ኢፒኤ ክልል 3 (U.S. EPA Region 3) ጋር የተያያዙ የማስፈጸም ስራዎች ላይ እንደ መሪ የግንኙነት ኤጀንሲ በመሆን ያገለግላል። በተጨማሪ፣ ቢሮው የሚመለከታቸው ማህበረሰቦች ላይ ስምሪት በማድረግ የዲዲኦዲ(DOEE)ን የአከባብያዊ ፍትሕ ተነሳሽነተ ያስፈጽማል።

የማህበራዊ ግንኝነቶች ቢሮ ለዲዲኦኢ(DOEE) የህዝባዊ ስምሪት እና የማህበረሰባዊ ትምህርት ፕሮግራሞች ያካሂዳል። ኦሲአር (OCR) የኤጀንሲው ኦንላይን ህላዌ ያካሂዳል እና ያዳብራልም፤ እንዲሁም፣ የኤጀንሲው ፕሮግራሞች እና ዝግጅቶችን ያስተዋውቃል።

የሀይል አስተዳደ(ኢኤ) ለተለያዩ የመጨረሻ-ተጠቃሚ አካላት (እነዚህም የመኖርያ፣ ንግድ እና ድርጅት ቦታዎች) በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምብያ ያነሰ ሀይል እንዲጠቀሙ ለማድረግ፣ የሀይል ብቃት እና የሚታደስ ሀይል ዕቅዶች እና አገልግሎቶች ያቀርባል። በተጨማሪ፣ ኢኤ(EA) ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎችን የሀይል ወጪያቸውን ለመሸፈን ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ እና የዋጋ ቅናሽ ይሰጣል።
የአከባቢ አገልግሎቶች አስተዳደር(ኢኢስኤ) ፣ ለአገልግሎት ቦታዎች እና ለአገልግሎት ሰጪ ባለሙያዎች እውቅና በመስጠት፣ እቅዶችን በመገምገም፣ ፍቃዶችን በመስጠት፣ ምርመራን በማድረግ እና አዲስ መመርያ ፖሊሲዎችን በመጠቆም፣ በዲስትሪክቱ መሬት፣ አየር፣ ውሀ እና ቤቶች ሊኖር ለሚችለው መርዛማ ነገሮች እና በካዮች ለመቀነስ ይሰራል። ኢኤስኤ(ESA) የሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች የሊድ ምረዛ መከላከል፣ ጤነኛ ቤቶች፣ የአየር ጥራት፣ ተባይ ማጥፍያ፣ መርዛም ቆሻሻ፣ እና ከመሬት በታች መቋጠርያ ታንኮች የሚያካትቱ ናቸው። The Natural Resources Administration (የተፈጥሮአዊ ሀብት አስተዳደር) በዲስትሪክቱን የውሀ ውስጥ እና የዱር እንስሳ ሀብት፣ የውሀ ጥራት፣ ውሀ ከል መከላከል እና የዶፍ ውሀ ማኔጅመንት ይቆጣጠራል። ክፍሉ፣ ለንግድ ተቐማት፣ የፌደራል እና ዲስትሪክት መንግስታት፣ እና ለዲስትሪክት ነዋሪዎች የንግድ ፈቃድ ፣ ፍተሻ፣ መከታተል፣ ፈቃድ በመስጠት እና ቴክኒካዊ ድጋፍ በመስጠት ሰርቲፊኬሽን፤ ክለሳ እና ቴክኒካዊ ትንተና አገልግሎት ያቀርባል። በተጨማሪ፣ የተፈጥሮ ሀብቶች ትምህርት እና ስምሪት ይሰጣል፤ ተፈጥሮአዊ ሀብቶች ለመንከባከብ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ይጠቀማል።

አገልግሎቶች፦ የዲዲኦኢ(DOEE) የዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምብያ የአከባቢዊ ሁኔታ ደረጃ መመዘኛዎችን የሚያወጣ፣ የሚያውጅ እና የሚያስፈጽም፣ እና የፌደራልና የአከባቢ ህጎች እና መመሪያዎችን ለማስፈጸም በመሪነት የሚሰራ ኤጀንሲ ነው። የዲስትሪክቱ የአየር፣ ውሀ እና የመሬት ሀብት ጥራት በመከላከል እና ወደ ቀድሞው ሁኔታ ለመጠገን በሚያደርገው ዕለታዊ ስራው፣ በዚያውም የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች የኑሮ ጥራት ለማዳበር፣ ጤናማ ህብረተሰብ እንዲኖር በማድረግ፣ እና ብልሀዊ እና ዘላቂ እድገት በማስፋፋት በሚያደርገው ጥረት፣ የዲዲኦኢ(DOEE) ዋነኛ ሀላፊነቶች፣ ሌሎችንም ጨምሮ፣ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡ ፈቃዶች መስጠት፣ የአከባቢ ሁኔታዎች መከታተል፣ የገንዘብ እና ቴክኒካዊ ድጋፎች መስጠት፣ የአከባቢ አደጋ መመዘን፣ ዕቅዶች ማውጣት፣ ቦታዎች መመርመር ፣ የአከባቢ ህጎችን ማስፈጸም፣ የእለት-ተዕለት የአከባቢ ጉዳዮችን በተመለከተ ከሌሎች አካሎች ጋር ሆኖ መስራት፣ እና ህብረተሰቡን ስለ መንግስት አካሄዶች እና ጥቅሞች መንገር እና ማስተማር።

የትርጉም አገልግሎቶች፦ ዲዲኦኢ(DOEE) በዲስትሪክቱ የቋንቋ መስመር አገልግልቶች (Language Line Services) ይሳተፋል። ስለ ዲስትሪክት የአከበቢ ዲፓርትመንት አገልግሎቶች የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ ድህረገጽ www.doee.dc.gov መጎብኘት፣ ወይም በ(202) 535-2600 ስልክ ቁጥር መደወል ይቻላል። ተጨማሪ እርዳታ ሊሰጥዎ ወደሚችል አስተርጓሚ በቀጥታ ይገናኛሉ። በተጨማሪ፣ ዲስትሪክቱ ፍቃድ ከሰጣቸው በርከት ያሉ አገልግሎት ሰጪዎች ደግሞ የጽሑፍ ትርጉም አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።

አድራሻ፦ ዲስትሪክት የአከባቢ ዲፓርትመንት, 1200 First Street, NW 5th Floor, Washington, DC 20002

የመገልገያ አቅም ተመጣጣኝ ፕሮግራሞች

 

ለኪራይ ቤቶች የሌድ ማሳወቂያ ቅጽ